ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ሲራክ 46 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)ኢያሱ 1 የነነዌ ልጅ ኢያሱ፥ ጦረኛ፥ በትንቢትም ሥራ ሙሴን የተካ ነበር፥ እንደ ስሙ ሁሉ የሕዝብ አዳኝ በጠላቶቹ ላይ የበቀል ቅጣትን ያወረደ፥ እሥራኤልንም ለርስቱ ያበቃ ነው። 2 መሣሪያውን ሲያነሣ፥ በከተሞችም ላይ ሠይፉን ሲሰነዝር ምንኛ ደስ ያሰኛል፥ 3 የእርሱን ያህል ቆራጥነት ከቶ ያሳየ ይኖራልን? የእግዚአብሔርን ጦርነቶች የመራ እርሱ ነው። 4 ፀሐይ የታገተቸውና አንድም ቀን ሁለት የሆነው በእርሱ እጅ አልነበረምን? 5 ጠላትን በያቅጣጫው እያባረረ ሳለም ኃያሉንና ልዑል ጌታን ለመነ፥ እግዚአብሔርም ከባድና አስፈሪ በረዶን በማዝነብ መለሰለት። 6 ጠላት የሆነውን ሕዝብ ወጋ፥ በቁልቁለቱም ላይ ደመሰሳቸው፥ የእርሱን ጀግንነት በጌታ ስም እንደሚዋጋ አሳያቸው። ካሌብ 7 በሙሴ ዘመን ታማኝነቱን ያስመሰከረ፥ የኃያሉ እግዚአብሔር ተከታይ ነበር። እርሱና የዩፍኒ ልጅ ካሌብ ሕዝቡን በመቃወም፥ ኃጢአት እንዳይፈጽሙ በመጠበቅ፥ ዓመፃውንም በማብረድ ትክክለኛነታቸውን አሳይተዋል። 8 ወተትና ማር ወደሚፈስባት ርስታቸውም፥ በመመለስ ላይ ከነበሩት ስድስት መቶ ሺህ ሰዎች፥ መካከል ሁለቱ ብቻ ሊድኑ የቻሉትም በጽድቅ ሥራቸው ነበር። 9 ጌታ ለካሌብ እስከ እርጅናው ዘመን ያልከዳውን ብርታት ሰጠው፥ የወገኖቹ ርስት በሆነው በተራራማው ሀገርም ኃይሉን ሁሉ አዋለ። 10 ጌታን መከተል መልካም መሆኑንም እስራኤላውያን ከእርሱ ይማሩ። መሳፍንት 11 መሳፍንቱም ሁሉ እያንዳንዳቸው ሲጠሩ፥ ልባቸው ያልሸፈተ፥ በጌታም ላይ ጀርባቸውን ያላዞሩ፥ መታሰቢያቸው የተባረከ ይሁን። 12 ዓላማቸው ከመቃብራቸው በላይ ይለምልም! የነኝህ ታላላቅ ሰዎች ልጆችም፥ ያባቶቻቸውን ስም ለማደስ ያብቃቸው፤ ሳሙኤል 13 ሳሙኤል በጌታ የተወደደ ነቢይ፥ መንግሥቱንም ያቋቋመ፥ የሕዝቡንም መሪዎች የቀባ ነው። 14 በጌታ ሕግ መሠረት በጉባኤው ላይ ፈርዷል፥ ጌታም ያዕቆብን ጠበቀ። 15 በታማኝነቱም ነቢይነቱ ተቀባይነት አገኘ፤ በቃሉም እውነተኛ ነቢይ መሆኑን አስመሰከረ። 16 በሁሉም አቅጣጫ የጠላትን መግፋት ባየ ጊዜ፥ ጡት ያልተወች ጠቦት አርዶ መሠዋዕት በማቅረብ፥ ኃያሉንና ታላቁን ጌታ ተማፀነ። 17 ጌታ ከሰማይ አስገመገመ፥ ነጐድጓዳዊ ድምፁንም አሰማ፥ 18 የጠላት አለቆችን፥ ፍልስጥኤማውያን መሪዎችን ሁሉ አጠፋ 19 ወደ ዘላለማዊው ዕረፍቱ ከማምራቱም በፊት፥ ከማንም በላይ ቢሆን ጥንድ ጫማዎችን እንኳ አልወሰድኩም። ሲል በጌታና በመሢሑ ፊት ቃሉን ሰጥቷል፥ የከሰሰውም ሰው አልነበረም። 20 ከሞተም በኋላ የንጉሡን ፍጻሜ ተንብዮአል። የሕዝቡን ኃጢአት ለማጥፋት፥ በከርሰ መቃብርም ሆኖ ትንቢት ተናግሯል። |