በጓደኞችህና በወዳጆችህ ፊት ስትወሰልት፥ በጐረቤቶችህም ፊት ስትሰርቅ፥ እፍረት ይሰማህ።
ለእንግዳ በእንግድነት ካደረበት ቤት ሰርቆ መሄድ ኀፍረት ነው፤ የእግዚአብሔርንም እውነትና ቃል ኪዳን ማፍረስ ኀፍረት ነው፤ የሌላ ሰው እህል ለመብላት በመስገብገብ መቅረብ ኀፍረት ነው፤ አደራ ከአስጠበቁህ ገንዝብና ከባልንጀራህ ገንዘብ መስረቅ ኀፍረት ነው።