ሞት ሆይ! ንብረቱን እንደ ያዘ በሰላም ለሚኖር፥ ያለአንዳች ጭንቀት ኑሮውን ለሚመራና በምግብም ለሚደሰት ሰው አንተን ማሰብ ምንኛ ያሰቅቃል!
ሞት ሆይ፥ ሰው በደኅና ሲኖር፥ በሁሉ ተዘጋጅቶ ሳለ፥ ኀይልም ሳለው፥ ለመብላትም ሆዱ ተከፍቶ ሳለ፥ በሰው ላይ በምትመጣ ጊዜ ስም አጠራርህ እንዴት መራራ ነው!