መልካም ውጤት ያስገኛል ብለህ ካመንክ ከመናገር ወደኋላ አትበል ጥበብህንም አትደብቅ፤
የሚናገርን ሰው መናገሩን አትከልክለው፤ ከቃሉ የተነሣ ጥበቡ ይታወቃልና፥ ትምህርቱም ከአንደበቱ ንግግር የተነሣ ይታወቃልና።