ሮሜ 4:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መተላለፋቸው ይቅር የተባለላቸው፥ ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው የተባረኩ ናቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “መተላለፋቸው ይቅር የተባለላቸው፣ ኀጢአታቸው የተሰረየላቸው፣ ብፁዓን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በደላቸው ይቅር የተባለላቸውና ኃጢአታቸው የተደመሰሰላቸው ሰዎች የተባረኩ ናቸው! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “መተላለፋቸው የቀረላቸው፥ ኀጢአታቸውም የተሰረየላቸው ብፁዓን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤ |