መዝሙር 85:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በጎ ነገርን ይሰጣል፥ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፤ ለአረማመዱም መንገድ ያዘጋጃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈለጉን እንከተል ዘንድ ጽድቅ በእግዚአብሔር ፊት ይሄዳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሕረትህ በእኔ ላይ ታላቅ ናትና፥ ነፍሴንም ከታችኛዪቱ ሲኦል አድነሃታልና። |
እኛም ሁላችን፥ በመጋረጃ በማይሸፈን ፊት፥ የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን፥ የእርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፥ ይህም መንፈስ ከሚሆን ጌታ የመጣ ነው።
ክርስቶስ በእኔ ይኖራል እንጂ ከእንግዲህ ወዲያ እኔ አልኖርም፤ አሁን በሥጋ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ በማመን የምኖረው ነው።
እንግዲህ ክርስቶስ በሥጋ ስለ እኛ መከራን በመቀበሉ፥ እናንተም በዚህ ሐሳብ ራሳችሁን አስታጥቁ፤ ምክንያቱም በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአል።