እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
መዝሙር 74:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጠን ወደሌላቸው ፍርስራሶች እርምጃህን አቅና፥ ጠላት በመቅደስ ያለውን ሁሉ አጥፍቶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርምጃህን ለዘላለሙ ባድማ ወደ ሆነው አቅና፤ ጠላት በመቅደስህ ውስጥ ያለውን ሁሉ አበላሽቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጠላቶቻችን ለዘለቄታ የፈራረሰውን ቤተ መቅደሱን ተዘዋውረህ ተመልከትልን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድርና በእርስዋ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ ቀለጡ፥ እኔም ምሰሶዎችዋን አጸናሁ። |
እርሱም ቤተ መቅደሱን፥ ቤተ መንግሥቱን፥ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ የታላላቅ ሰዎችን ቤቶችና በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤
እነርሱም፦ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ትሩፋን በታላቅ መከራና በመሰደብ ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
በሌሊትም በሸለቆው በር ወጣሁ፥ ወደ “የዘንዶ ምንጭ” እና ወደ “የፍግ በር” ሄድኩ፤ የፈረሰውን የኢየሩሳሌምን ቅጥርና በእሳት የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትኩ።
ንጉሡንም እንዲህ አልሁት፦ “ንጉሡ ለዘለዓለም ይኑር! የአባቶቼ መቃብር ያለባት ከተማ ስትፈርስ፥ በሮችዋም በእሳት ሲቃጠሉ ፊቴ ለምን አያዝን?”
ሀብታቸውን እንዲዘርፍ፤ ምርኮን እንዲያግበሰብስ፤ እንደ መንገድ ላይ ጭቃም እንዲረግጣቸው፤ አምላክ በሌለው ሕዝብ ላይ እልከዋለሁ፤ በሚያስቆጣኝም ሕዝብ ላይ እሰደዋለሁ።
ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ፥ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደገና ይሠራሉ።
እነዚያንም ነገሥታት ወደ ኢያሱ ባወጡአቸው ጊዜ ኢያሱ የእስራኤልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፥ ከእርሱም ጋር የሄዱትን የተዋጊዎቹን የጦር አዛዦች እንዲህ አላቸው፦ “ቅረቡ፥ በእነዚህም ነገሥታት አንገት ላይ እግራችሁን አኑሩ።” ቀረቡም በአንገታቸውም ላይ እግራቸውን አኖሩ።
ከመቅደሱ ውጭ ያለውን አደባባይ ግን ተወው፤ አትለካውም፥ ምክንያቱም ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና፤ እነርሱም ለአርባ ሁለት ወር ያህል የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።