የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ ደስ ይበላቸው፥ ማዳንህን የሚወድዱ ሁልጊዜ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ።
እኔ ግን ችግረኛና ድኻ ነኝ፤ አምላክ ሆይ፤ ፈጥነህ ድረስልኝ፤ አንተ ረዳቴና፣ ታዳጊዬም ነህና፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አትዘግይ።
እኔ ጐስቋላና ምስኪን ነኝ፤ አምላክ ሆይ! ፈጥነህ ወደ እኔ ና፤ እግዚአብሔር ሆይ! ረዳቴና አዳኜ አንተ ስለ ሆንክ አትዘግይ!
አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ ጌታዬ ሆይ፥ ከታናሽነቴ ጀምሬ ተስፋ አደረግሁህ።
እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥ በውስጤም ልቤ ቆስሎአል።
የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ በፍጥነት ድረስልኝ፥ ወደ አንተ ስጮኽም የልመናዬን ድምፅ ስማ።
አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፥ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ ዘወትር፦ ጌታ ታላቅ ይሁን ይበሉ።
ከሕያዋን መጽሐፍ ይደምሰሱ፥ ከጻድቃንም ጋር አይጻፉ።
ምክንያቱም ገና “በጣም ጥቂት ጊዜ፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል፥ አይዘገይምም፤
ይህን የሚመሰክር “አዎን በቶሎ እመጣለሁ፤” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።