Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 40:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፥ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ ዘወትር፦ ጌታ ታላቅ ይሁን ይበሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እኔ ግን ችግረኛና ድኻ ነኝ፤ ጌታ ግን ያስብልኛል። አንተ ረዳቴና ታዳጊዬም ነህና፤ አምላኬ ሆይ፤ አትዘግይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 አምላክ ሆይ! እኔ ችግረኛ ድኻ ነኝ፤ አንተ ግን አልረሳኸኝም፤ አንተ ረዳቴና አዳኜ ስለ ሆንክ አሁንም በፍጥነት እርዳኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 40:17
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ ደስ ይበላቸው፥ ማዳንህን የሚወድዱ ሁልጊዜ፦ እግዚአብሔር ታላቅ ነው ይበሉ።


ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፥ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ ጌታ እሰማቸዋለሁ፥ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።


ስለዚህ በመተማመን፥ “ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል?” እንላለን።


ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም በፍጹም አያፍርም።


እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።


አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ የአፌንም ቃል አድምጥ፥


ጌታን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ባለጸጋ እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱም ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


የዳዊት ጸሎት አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ደሃና ችግረኛ ነኝና።


ችግረኞች ያያሉ ደስ ይላቸዋል፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ ሕያዋንም ሁኑ።


ይህን የሚመሰክር “አዎን በቶሎ እመጣለሁ፤” ይላል። አሜን፤ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤


የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ ታውቃላችሁ፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።


ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጉድጓድ፥ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት የለውም፤” አለው።


እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥ በውስጤም ልቤ ቆስሎአል።


ጌታን ከእኔ ጋር አክብሩት፥ በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።


ጽድቄን የሚወድዱአት ደስ ይበላቸው ሐሴትንም ያድርጉ፥ የባርያውን ሰላም የሚወድድ ጌታ ታላቅ ይሁን ዘወትር ይበሉ።


በዚያም ቀን፦ እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፥ ያድነንማል፤ ጌታ ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ይባላል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች