በመኝታዬም አስብሃለሁ፥ በማለዳም ስለ አንተ አሰላስላለሁ፥
አንተ ረዳቴ ነህና፣ በክንፎችህ ሥር ተጠልዬ በደስታ እዘምራለሁ።
አንተ ረዳት ስለ ሆንከኝ በጥበቃህ ሥር ተጠልዬ፥ በደስታ እዘምራለሁ።
እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል። መቅሠፍታቸው እንደ ልጆች ሕንፃ ሆነ፤
እንደ ዐይን ብሌን ጠብቀኝ፥ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባርያህ ፈቀቅ አትበል፥ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተወኝ።
አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፥ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አስወግዳቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብሃልና።
ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
በጠላት ፊት ጽኑ ግንብ፥ መጠጊያዬም ሆነኸኛልና።
እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በእርሱ ላይ ጥለናል።
ከአንበሳ መዳፍና ከድብ መንጋጋ ያዳነኝ ጌታ አሁንም ከዚህ ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል።” ሲል ዳዊት ተናገረ። ሳኦልም ዳዊትን፥ “ሂድ፤ ጌታ ካንተ ጋር ይሁን!” አለው።