Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 21:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ንጉሥ በኀይልህ ደስ ይለዋል፤ በምትሰጠውም ድል እጅግ ሐሤት ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 አምላክ ሆይ! ኀይልን ስለ ሰጠኸው ንጉሥ ደስ ብሎታል፤ ድልን ስለ አቀዳጀኸውም ሐሴት ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አም​ላኬ፥ አም​ላኬ፥ ተመ​ል​ከ​ተኝ፥ ለምን ተው​ኸኝ? የኀ​ጢ​አቴ ቃል እኔን ከማ​ዳን የራቀ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 21:1
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።


እንዲህም አሉ፦ “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና።”


እርሱ ዓለቴም መድኃኒቴም ነውና፥ እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ አልታወክም።


ጌታ ኃይሌና ጋሻዬ ነው፥ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፥ ልቤም ደስ ይለዋል፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ።


እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ።


ፍርድን የምትወድ ኃያል ንጉሥ፥ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ በያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ ፈጽምህ።


ኑ፥ በጌታ ደስ ይበለን፥ ለመዳናችን ዓለት እልል እንበል።


አምላኬ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፥ እስከ ዛሬም ተኣምራትህን እነግራለሁ።


ለሰይፍ እጅ አልፈው ይሰጣሉ፥ የቀበሮም እድል ፈንታ ይሆናሉ።


እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፥ እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች