ልብህ ተጸጽቶአልና፥ በፊቴም ራስህን አዋርደሃልና፥ በዚህም ስፍራና በነዋሪዎችዋ ላይ የተናገርሁትን ቃላቴን በሰማህ ጊዜ ራስህን አዋርደሃልና፥ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ፥ ይላል ጌታ።
መዝሙር 6:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ ጌታ የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ልመናዬን ሰምቷል፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ይቀበላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ልመናዬን ያዳምጣል፤ እግዚአብሔር ለጸሎቴ መልስ ይሰጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማኝ፤ እግዚአብሔር ጸሎቴን ተቀበለ። |
ልብህ ተጸጽቶአልና፥ በፊቴም ራስህን አዋርደሃልና፥ በዚህም ስፍራና በነዋሪዎችዋ ላይ የተናገርሁትን ቃላቴን በሰማህ ጊዜ ራስህን አዋርደሃልና፥ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ አልቅሰሃልና እኔ ደግሞ ሰምቼሃለሁ፥ ይላል ጌታ።
“ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ።