Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 6:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ዓይኔ ከኀዘን ዕንባ የተነሣ ታወከች፥ ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ ደከመች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እናንተ ክፉ አድራጊዎች ሁሉ፤ ከእኔ ራቁ፤ እግዚአብሔር የልቅሶዬን ድምፅ ሰምቷልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር የለቅሶዬን ጩኸት ሰምቶአል፤ ስለዚህ እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ዐመ​ፃን የም​ታ​ደ​ርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​ቅ​ሶ​ዬን ቃል ሰም​ቶ​አ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 6:8
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘች፥ መላ ሰውነቴ እንደ ጥላ ሆነ።


በእርግጥም ነፍሴን ከሞት፥ ዓይኔንም ከእንባ፥ እግሬንም ከመሰናከል አድነሃል።


እናንተ ኃጢአተኞች፥ ከእኔ ራቁ፥ የአምላኬንም ትእዛዝ ልፈልግ።


አቤቱ፥ አንተ ክፉዉን የምትገድል ከሆንህስ፥ የደም ሰዎች ሆይ፥ “ከእኔ ፈቀቅ በሉ”።


ጌታ ለሚጠሩት ሁሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።


አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ጋሻዬ ነህ፥ ክብሬና ራሴንም ቀና የምታደርገው አንተ ነህ።


ተቸግሬአለሁና አቤቱ ምራኝ፥ ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ደከመ፥ ነፍሴም ሆዴም።


መቼም አታድናቸውም! አቤቱ አሕዛብን በቁጣ ጣላቸው።


በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖር ሕዝብ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅስም፤ በጩኸትም ድምፅ ይራራልሃል፥ በሰማህም ጊዜ ይመልስልሃል።


“ጌታ ሆይ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ።” ሕዝቅያስም እጅግ አድርጎ አለቀሰ።


“ሂድ፥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ።


ድምፄን ሰማህ፥ ጆሮህን ከልመናዬ አትመልስ።


ከዚህ በኋላ በግራው ያሉትን ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ።


ያንጊዜ ‘ከቶ አላውቃችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ’ እላቸዋለሁ።


እርሱም ‘እላችኋለሁ፥ ከየት እንደ ሆናችሁ አላወቅም፤ ዐመፀኞች በሙሉ፥ ከእኔ ራቁ፤’ ይላችኋል።


እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች