መዝሙር 59:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፥ አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአፋቸው ስለሚወጣው ኀጢአት፣ ከከንፈራቸውም ስለሚሰነዘረው ቃል፣ በትዕቢታቸው ይያዙ። ስለ ተናገሩት መርገምና ውሸት፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንደበታቸው ኃጢአት አይጠፋም፤ ንግግራቸው ሁሉ ኃጢአት የሞላበት ነው፤ እነርሱ ስለሚራገሙና ስለሚዋሹ በትዕቢታቸው ይያዙ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ኀይልን እናደርጋለን፤ እርሱም የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋል። |
በሚሄዱባቸው አሕዛብ መካከል ርኩሰታቸውን ሁሉ እንዲናገሩ ከእነርሱ ጥቂቶች ከሰይፍ፥ ከራብና ከቸነፈር አስቀራለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።
በዚያ ቀን በእኔ ላይ አምፀሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም፤ በኩራትሽ የተደሰቱትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ላይ ዳግመኛ አትታበዪም።