Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 10:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አፉ በመርገም፥ በሽንገላና በዐመፃ የተመላ ነው፥ ከምላሱ በታች ተንኰልና ክፋት አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 አፉ መርገምን፣ ቅጥፈትንና ግፍን የተሞላ ነው፤ ሽንገላና ክፋት ከምላሱ ሥር ይገኛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ንግግሩም በእርግማን፥ በሐሰትና በዛቻ የተሞላ ነው፤ ተንኰልና ክፉ ነገር በአንደበቱ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድ​ቅ​ንም ይወ​ድ​ዳል፤ ቅን​ነት ግን ፊቱን ታየ​ዋ​ለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 10:7
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጉዳትን ይፀንሳሉ፥ በደልንም ይወልዳሉ፥ ሆዳቸውም ተንኰልን ያዘጋጃል።”


“ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፥ ከምላሱም በታች ቢሰውረው፥


አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።


በልባቸውም ክፉ ካሰቡ፥ ቀኑን ሁሉ ለሰልፍ ከሚከማቹ።


አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለክፉዎች አትስጠኝ፥ ተንኮላቸው እንዲሳካ አትፍቀድ።


አድነኝ፥ አፋቸውም ምናምንን ከሚናገር፥ ቀኛቸውም የሐሰት ቀኝ ከሆነ፥ ከባዕድ ልጆች እጅ አስጥለኝ።


እራሱን ሸንግሎአልና፥ ኃጢአቱን መቀበልና መጥላት ይሳነዋል።


ጠላቶቼም በላዬ ክፋትን ይናገራሉ፦ መቼ ይሞታል ስሙስ መቼ ይሻራል? ይላሉ።


አቤቱ፥ በጠላቶቼ ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ፥ መንገዴን በፊትህ አቅና።


አፍህ ክፋትን አበዛ፥ አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ።


አንደበትህ ጥፋትን ያስባል፥ እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግህ።


ወዳጄ ከእርሱ ጋር ሰላም በነበሩት ላይ እጁን ዘረጋ፥ ኪዳኑንም አፈረሰ።


በልባችሁ በምድር ላይ ግፍን ትሠራላችሁና፥ እጆቻችሁም ዐመጽን ይፈጽማሉና።


ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፥ አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም።


ስለ አፋቸው ኃጢአት ስለ ከንፈራቸውም ቃል፥ መርገምንና ሐሰትን ስለሚናገሩ፥ በትዕቢታቸው ይጠመዱ።


እስከ መቼ በሰው ላይ ትነሣላችሁ? እናንተ ሁላችሁ እንዳዘነበለ ግድግዳ እንደ ፈረሰም ቅጥር ትገድላላችሁ።


ከክፉዎች ደባ፥ ከዓመፀኞችም ብዛት ሰውረኝ።


የሞት መሣርያንም አሰናድቷል፥ ፍላጻዎቹንም የሚንበለበሉ አደረገ።


በሹፈት ክፉ ነገርን ተናገሩ። ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ።


በሐሰተኛ ምላስ መዝገብ ማከማቸት የሚበንን ጉም ነው፥ ይህን የሚፈልጉ ሞትን ይፈልጋሉ።


ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው፥ ድህነትንና ሀብታምነትን አትስጠኝ፥ የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ፥


በጽድቅ የሚጠራ በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በእርባና ቢስ ነገር ታምነዋል ሐሰትንም ተናግረዋል፤ ጉዳትን ፀንሰዋል በደልንም ወልደዋል።


ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።


ማደሪያህ በሽንገላ መካከል ነው፥ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ለማወቅ እንቢ ብለዋል፥ ይላል ጌታ።


ችግረኛውን የምትረግጡ፥ የአገሩንም ድሀ የምታጠፉ ይህን ስሙ፤


እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ነገር ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ የሞላውን አፍ ይናገራልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች