አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።
መዝሙር 148:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታን ስም ያመስግኑ፥ ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና፥ ክብሩም በሰማይና በምድር ላይ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣ ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣ እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእርሱ ስም ከሌሎች ስሞች ስለሚበልጥና ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ከፍ ያለ ስለ ሆነ ሁሉም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርን ስም ያመሰግናሉ። ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ በሰማይና በምድር ያመሰግኑታል። |
አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።
አንቺ በሴቶች ዘንድ የተዋብሽ ሆይ፥ ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ፍቅረኛሽ ምን አለው? ይህን የሚያህል የምታስምይን? ከሌላ ወዳጅ ይልቅ ፍቅረኛሽ ምን አለው?
አዎን፤ በእውነት ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ጌታዬ ለማወቅ ስል ሁሉ ነገር ጉዳት እንደሆነ አድርጌ እቈጥራለሁ፤ ስለ እርሱ ሁሉን ነገሮች በማጣት ተጐዳሁ፤ እነርሱንም እንደ ጉድፍ አድርጌ ቈጠርኋቸው፤ በዚህም ክርስቶስን እንዳገኝ፥