Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 148:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ያመ​ሰ​ግ​ናሉ። ስሙ ብቻ​ውን ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፥ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣ ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣ እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የጌታን ስም ያመስግኑ፥ ስሙ ብቻውን ከፍ ከፍ ብሏልና፥ ክብሩም በሰማይና በምድር ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 የእርሱ ስም ከሌሎች ስሞች ስለሚበልጥና ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ከፍ ያለ ስለ ሆነ ሁሉም የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 148:13
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያለው ሁሉ የአ​ንተ ነውና ታላ​ቅ​ነ​ትና ኀይል፥ ክብ​ርም፥ ድልና ጽንዕ የአ​ንተ ነው፤ ነገ​ሥ​ታ​ቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊ​ትህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


በወ​ደ​ድ​ኋ​ቸው ፋንታ አጣ​ሉኝ፥ እኔ ግን እጸ​ል​ያ​ለሁ።


ተራ​ሮች እንደ ኮር​ማ​ዎች፥ ኮረ​ብ​ቶ​ችም እንደ በጎች ጠቦ​ቶች ዘለሉ።


እስ​ት​ን​ፋስ ያለው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ስ​ግ​ነው። ሃሌ ሉያ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥር​ሳ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው ውስጥ ይሰ​ብ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ን​በ​ሶ​ቹን መን​ጋ​ጋ​ቸ​ውን ያደ​ቅ​ቃል።


እን​ዴት ለጥ​ፋት ሆኑ! በድ​ን​ገት አለቁ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ጠፉ።


አቤቱ ጌታ​ችን፥ ስምህ በም​ድር ሁሉ እጅግ ተመ​ሰ​ገነ፥ ምስ​ጋ​ናህ በሰ​ማ​ዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።


ከሕ​ፃ​ና​ትና ከሚ​ጠቡ ልጆች አፍ ምስ​ጋ​ናን አዘ​ጋ​ጀህ፥ ስለ ጠላት፥ ጠላ​ት​ንና ግፈ​ኛን ታጠ​ፋው ዘንድ።


አቤቱ፥ ጌታ​ችን፥ ስምህ በም​ድር ሁሉ እጅግ ተመ​ሰ​ገነ።


ጕሮ​ሮው እጅግ ጣፋጭ ነው፥ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም የተ​ወ​ደደ ነው፤ እና​ንተ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቈነ​ጃ​ጅት ሆይ፥ ልጅ ወን​ድሜ ይህ ነው፥ ወዳ​ጄም ይህ ነው።


አንቺ በሴ​ቶች ዘንድ የተ​ዋ​ብሽ ሆይ፥ ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው? ይህን ያህል መሐላ አም​ለ​ሽ​ና​ልና ከወ​ን​ድ​ሞች ልጆች ይልቅ ልጅ ወን​ድ​ምሽ ማን ነው?


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ትላ​ላ​ችሁ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ስሙ​ንም ጥሩ፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ክብ​ሩን አስ​ታ​ውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስ​ታ​ውሱ።


በአ​ር​ያም የሚ​ኖር ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይኖ​ራል፤ ጽዮ​ንም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ተሞ​ላች።


አን​ዱም ለአ​ንዱ፥ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ምድር ሁሉ ከክ​ብሩ ተሞ​ል​ታ​ለች” እያለ ይጮኽ ነበር።


በጎነቱ እንዴት ታላቅ ነው! ውበቱስ እንዴት ታላቅ ነው! እህል ጐበዛዝቱን፥ ጉሽ ጠጅም ቈነጃጅቱን ያለመልማል።


ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።’


የወ​ረ​ደው እርሱ ነው፤ ሁሉ​ንም ይመላ ዘንድ ከሰ​ማ​ያት ሁሉ በላይ የወ​ጣው ደግሞ እርሱ ነው።


ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግ​ለው ዘንድ፥ ሁሉን የተ​ው​ሁ​ለት፥ እንደ ጕድ​ፍም ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት የጌ​ታ​ዬን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ኀይ​ልና ገና​ና​ነት ስለ​ማ​ውቅ ሁሉን እንደ ኢም​ንት ቈጠ​ር​ሁት።


እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች