መራገምን ወደደ፥ ወደ እርሱም መጣች፥ በረከትንም አልመረጠም፥ ከእርሱም ራቀች።
መራገምን ወደደ፤ ወደ እርሱም መጣች፤ በመባረክ ደስ አልተሠኘም፤ በረከትም ከርሱ ራቀች።
መራገም ይወድ ስለ ነበር፥ እርሱም የተረገመ ይሁን፤ መመረቅን ይጠላ ስለ ነበር፥ እርሱንም የሚመርቅ ሰው አይኑር።
እርሱም መልሶ እንዲህ አለ፦ ‘ወጥቼ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ።’ ጌታም እንዲህ አለው፦ ‘ታታልለዋለህ፤ ይከናወንልሃል፤ ውጣ፥ እንዲህም አድርግ።
ልቡን ከጽድቅ የሚመልስ ሰው ከመንገዱ ፍሬ ይጠግባል፥ ጻድቅም ሰው ደግሞ በራሱ።
የልብ ዕውርነትንና እርግማንህን ትሰጣቸዋለህ።
ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ ለደም አሳልፌ እሰጥሃለሁ ደምም ያሳድድሃል፥ ደምን ስላልጠላህ ደም ያሳድድሃል።
በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል።
የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤”