ሮቤልም መልሶ፥ “በዚህ ልጅ ላይ፥ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።
መዝሙር 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ስለምን እግዚአብሔርን ናቀ? በልቡም፦ “ፈልጎ አያገኘኝም” ይላልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው በእግዚአብሔር ላይ ለምን ክፉ ይናገራል? በልቡስ፣ “ስለ ሥራዬ አይጠይቀኝም” ለምን ይላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ለምን አያከብሩህም? ለምንስ በልባቸው “እግዚአብሔር አይቀጣንም” ይላሉ? |
ሮቤልም መልሶ፥ “በዚህ ልጅ ላይ፥ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።
እንዲሁም ንጉሡ ኢዮአስ ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፥ ልጁንም ዘካርያስን አስገደለው፤ እርሱም ሲሞት፦ “ጌታ ይየው፥ ይበቀለውም” አለ።
ነገር ግን በመካከላችሁ ያለውን ጌታን ትታችሁታልና፥ በፊቱም፦ ‘ለምን ከዚያ ከግብጽ ወጣን?’ ብላችሁ አልቅሳችኋልና በአፍንጫችሁ እስኪ ወጣ እስኪያቅለሸልሻችሁም ድረስ ወር ሙሉ ትበሉታላችሁ።”
የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከጌታ ከእግዚአብሔር የሚመልስ ወንድም ሆነ ሴት ቤተሰብም ሆነ ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፤ ከመካከልህ እንዲህ ያለውን መርዘኛና መራራ የሆነ ፍሬ የሚያበቅል አይገኝባችሁ።