Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 10:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አቤቱ አምላክ ሆይ፥ ተነሥ እጅህንም ከፍ ከፍ አድርግ፥ ድሆችን አትርሳ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፤ አምላክ ሆይ፤ ክንድህን አንሣ፤ ረዳት የሌላቸውንም አትርሳ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር ሆይ፥ ተነሥ! አምላክ ሆይ፥ ኀያል ክንድህን አንሣ! የተጨቈኑትንም ችላ አትበላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 10:12
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያ ቀን ይላል ጌታ፦ ፈረሶችህን ከመካከልህ አጠፋለሁ፥ ሰረገሎችህንም እደመስሳለሁ፤


በጽዮን ለሚኖር ለጌታ ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል ድንቅ ሥራውን ንገሩ፥


“አሁን እነሣለሁ” ይላል ጌታ፥ “አሁን እከበራለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ።


አቤቱ ጌታ፥ እጅህ ከፍ ከፍ አለች አላዩም፤ ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ እሳትም ጠላቶችህን ትበላለች።


የምድር ፈራጅ ሆይ፥ ተነሥ፥ ለትዕቢተኞች ፍዳቸውን ክፈላቸው።


የሚያምኑህን ከሚቃወሙ በቀኝህ የምታድናቸው፥ ቸርነትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው።


ለዘለዓለምስ ርኅራኄው ተቈረጠችን? የሰጠውስ ቃል ኪዳን ለዘመናት አልቆአልን?


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።


ድሀ ለዘለዓለም አይረሳምና፥ የችግረኞችም ተስፋቸው ለዘለዓለም አይጠፋም።


ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት።


የሚከቡኝን አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።


ሳምሶንም ወደ ጌታ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ አምላክ ሆይ፤ እባክህን አንድ ጊዜ ብቻ ብርታት ስጠኝና ስለ ጠፉት ዐይኖቼ ፍልስጥኤማውያንን አንዴ ልበቀላቸው።”


ደምን የሚበቀል እርሱ አስቦአልና፥ የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና።


አቤቱ፥ ተነሥ፥ ቀድመህ ወደ ታች ጣለው፥ ነፍሴን ከኃጢአተኛ በሰይፍህ አድናት።


የምትገዛልህን እርግብ ለአራዊት አትስጣት፥ የችግረኞችህን ነፍስ መቼውንም አትርሳ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች