ምሳሌ 5:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍጻሜዋ ግን እንደ እሬት የመረረ ነው፥ ሁለት አፍ እንዳለው ሰይፍም፥ የተሳለ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጨረሻ ግን እንደ እሬት ትመርራለች፤ ሁለት አፍ እንዳለውም ስል ሰይፍ ትሆናለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጨረሻ ግን እርስዋ እንደ እሬት የመረረችና ሁለት አፍ እንዳለው ስለታም ሰይፍ የምትቈርጥ ነች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍጻሜው ግን እንደ ሐሞት የመረረ ነው፥ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅም የተሳለ ነው። |
እኔም ከሞት ይልቅ የመረረ ነገር መርምሬ አገኘሁ፤ እርሷም ልብዋ ወጥመድና መረብ የሆነ፥ እጆችዋም እግር ብረት የሆኑ ሴት ናት፥ በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነ ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛ ግን ይጠመድባታል።
የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፤ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፤ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም አሳብና ትኩረት ይመረምራል፤