ምሳሌ 9:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ነገር ግን እርሱ ሙታን ከዚያ እንዳሉ፥ ተጋብዦችዋም በሲኦል ጥልቀት ውስጥ እንዳሉ አያውቅም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 እነርሱ ግን ሙታን በዚያ እንዳሉ፣ ተጋባዦቿም በሲኦል ጥልቀት ውስጥ እንደ ሆኑ አያውቁም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 እርሱም ወደ ቤትዋ የሚሄዱ ሁሉ እንደሚሞቱና እስከ አሁንም ወደ ቤትዋ የገቡ ወደ ሙታን ዓለም ተሽቈልቊለው እንደወረዱ አያውቅም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ነገር ግን እርሱ ከኀያላን ወገን በእርሷ ዘንድ የሚጠፉ እንዳሉ፥ የሲኦል ወጥመድም በቤቷ እንደሚገኝ አያውቅም። ነገር ግን ፈጥነህ ሂድ፥ በቦታዋም አትዘግይ፥ የባዕድን ውኃ እንደምትሻገር በዐይንህ ወደ እርሷ መመልከትን አታዘውትር። ከባዕድ ውኃ ራቅ፥ ብዙ ዘመን ትኖር ዘንድ ከባዕድ ምንጭ ውኃ አትጠጣ። የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል። ምዕራፉን ተመልከት |