የጠገበች ነፍስ የማር ወላላ ትረግጣለች፥ ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር እንኳ ጣፋጭ ነው።
ለጠገበ ማር አይጥመውም፤ ለተራበ ግን እሬት እንኳ ይጣፍጠዋል።
የጠገበ ሰው ማር. አይጥመውም፤ የራበው ሰው ግን መራራው ነገር እንኳ ይጣፍጠዋል።
ሰውነቴ ትነካው ዘንድ እንቢ አለችው፥ እንደሚያስጸይፍ መብል ሆነብኝ።
ልጄ ሆይ፥ መልካም ነውና ማር ብላ፥ ወለላም ለጣምህ ጣፋጭ ነው።
የወዳጅ ማቁሰል ለክፉ አይሰጥም፥ የጠላት መሳም ግን የውሸት ነው።
ከቦታው ርቆ የሚሄድ ሰው ከጎጆዋ ርቃ እንደምትበርር ወፍ ነው።
ሕዝቡም በጌታና በሙሴ ላይ እንዲህ ብለው ተናገሩ፦ “በምድረ በዳ እንድንሞት ከግብጽ ለምን አወጣችሁን? እንጀራ የለም፥ ውኃም የለም፤ ሰውነታችንም ይህን የሚያንገሸግሽ እንጀራ ተጸየፈ።”
“አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን ለዚህ ሁሉ ሰው ምን ይሆናል?”