Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ምሳሌ 24:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ልጄ ሆይ፥ መልካም ነውና ማር ብላ፥ ወለላም ለጣምህ ጣፋጭ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ልጄ ሆይ፤ መልካም ነውና ማር ብላ፤ የማር ወለላም ጣዕም ይጣፍጥሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ልጄ ሆይ! መልካም ስለ ሆነ ማር. ብላ፤ የማር ወለላ ለምላስህ ጣፋጭ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ልጄ ሆይ፥ ማር ብላ፥ ወለላ ጕሮሮህን ያጣፍጥልህ ዘንድ መልካም ነውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ምሳሌ 24:13
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቃልህ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው፥ ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።


ጌታን መፍራት ንጹሕ ነው፥ ለዘለዓለም ይኖራል፥ የጌታ ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ናቸው።


ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፥ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።


በጣም እንዳትጠግብና እንዳትተፋው፥ ማር ባገኘህ ጊዜ የሚበቃህን ብላ።


ብዙ ማር መብላት መልካም አይደለም፥ ክቡር ነገሮችን መፈለግ ግን የሚያስከብር ነው።


የጠገበች ነፍስ የማር ወላላ ትረግጣለች፥ ለተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር እንኳ ጣፋጭ ነው።


ሙሽራዬ ሆይ፥ ከከንፈሮችሽ ማር ይንጠበጠባል፥ ከምላስሽ በታች ማርና ወተት አለ፥ የልብስሽም መዓዛ እንደ ሊባኖስ መዓዛ ነው።


እኅቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ወደ ገነቴ ገባሁ፥ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ለቀምሁ፥ እንጀራዬን ከማሬ ጋር በላሁ፥ የወይን ጠጄን ከወተቴ ጋር ጠጣሁ። ባልንጀሮቼ ሆይ፥ ብሉ፥ ጠጡ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ እስክትረኩ ድረስ ጠጡ።


ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ሲችል ቅቤና ማር ይበላል።


የዮሐንስ ልብስ ከግመል ጠጉር የተሠራ ነበር፥ በወገቡም ጠፍር ይታጠቅ ነበር፤ ምግቡም አንበጣና የበረሓ ማር ነበር።


በእጁ ወስዶም መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ከወላጆቹም ጋር እንደተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነርሱም በሉ። ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን መሆኑን አልነገራቸውም ነበር።


ነገር ግን ዮናታን አባቱ ሕዝቡን በመሐላ ማሰሩን አልሰማም ነበር። ስለዚህ በእጁ የያዘውን ዘንግ ጫፍ በማሩ ወለላ ውስጥ በማስገባት እጁን ወደ አፉ አደረገ፤ ዐይኑም በራ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች