Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 6:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 “አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን ለዚህ ሁሉ ሰው ምን ይሆናል?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ዐምስት ትንንሽ የገብስ እንጀራና ሁለት ትንንሽ ዓሣ የያዘ አንድ ልጅ እዚህ አለ፤ ይህ ግን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ እንዴት ይዳረሳል?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ አንድ ልጅ እዚህ አለ፤ ነገር ግን ይህ ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምን ይበቃል?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 “አም​ስት የገ​ብስ እን​ጀ​ራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላ​ቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነ​ዚህ ይህን ለሚ​ያ​ህል ሰው ምን ይበ​ቃሉ?”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነዚህን ለሚያህሉ ሰዎች ይህ ምን ይሆናል? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 6:9
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህም በቀር እያንዳንዱ ገዢ እንደ አስፈላጊነቱ የሚደርስበትን ሠረገላ ለሚስቡ ፈረሶችና ሌላም አገልግሎት ለሚያበረክቱ የጋማ ከብቶች ገብስና ገፈራ ያቀርብ ነበር።


ኤልሳዕም “እግዚአብሔር የሚለውን ስማ! ነገ ይህን ጊዜ በሰማርያ ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ይሸመታል” ሲል መለሰለት።


በወሰንሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ።


እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት፦ “እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን?


መላልሰው፥ እግዚአብሔርንም ተፈታተኑት፥ የእስራኤልንም ቅዱስ አሳዘኑት።


የጌታ ጠላቶችም በተገዙለት ነበር፥ ዘመናቸውም ለዘለዓለም በሆነ ነበር፥


ይሁዳና የእስራኤል ምድር ነጋዴዎችሽ ነበሩ፤ ዕቃዎችሽን በሚኒት ስንዴ፥ ጣፋጭ ዳቦ፥ ማር፥ ዘይትና በለሳን ይለውጡ ነበር።


እነርሱም “ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ በቀር በዚህ ምንም የለንም” አሉት።


አሁንም አታስተውሉምን? አምስቱ እንጀራ ለአምስት ሺህ በቅቶ ስንት መሶብ እንዳነሣችሁ አታስታውሱምን?


እርሱም፥ “ስንት እንጀራ አላችሁ? እስቲ ሄዳችሁ እዩ” አላቸው። አይተውም፥ “አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣ።”


አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺህ ሰው በቆረስሁ ጊዜ ስንት መሶብ ሙሉ ትርፍራፊ አነሣችሁ?” እነርሱም፥ “ዐሥራ ሁለት” አሉት።


እርሱ ግን፦ “እናንተ የሚበሉትን ስጡአቸው፤” አላቸው። እነርሱም፦ “ሄደን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን በቀር ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዓሣ የሚበልጥ የለንም፤” አሉት፤


ማርታም ኢየሱስን “ጌታ ሆይ! አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር፤


ማርያምም ኢየሱስ ወዳለበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ላይ ወድቃ “ጌታ ሆይ! አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተ ነበር፤” አለችው።


ኢየሱስም “አሁን ካጠመዳችሁት ዓሣ አምጡ” አላቸው።


ኢየሱስም መጣና እንጀራ አንሥቶ ሰጣቸው፤ እንዲሁም ዓሣውን።


ወደ የብስ በወጡ ጊዜ ዓሣ በላዩ የተቀመጠበት ፍምና እንጀራ አዩ።


ኢየሱስም እንጀራውን ያዘ፤ አመስግኖም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለተቀመጡት ሰዎች ሰጡአቸው፤ እንዲሁም ከዓሣው በፈለጉት መጠን።


ፊልጶስ “እያንዳንዳቸው ትንሽ ትንሽ እንኳ እንዲቀበሉ የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ አይበቃቸውም፤” ብሎ መለሰለት።


የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ ታውቃላችሁ፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።


የላሙንም ቅቤ፥ የመንጋውንም ወተት፥ ከሰቡት በጎችና ፍየሎች ጋር፥ የባሳንንም አውራ በጎች፥ ፍየሎችም፥ ከምርጥ ስንዴ ጋር በላህ፥ ከወይኑም ዘለላ የወይን ጠጅ ጠጣህ።”


የስንዴና ገብስ፥ የወይንና በለስ ዛፍ እንዲሁም ሮማን፥ የወይራ ዛፍና ማር ወደ ሞሉባት ምድር፥


በአራቱም ሕያዋን ፍጡራን መካከል እንደ ድምፅ ሰማሁ፦ “አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንን ግን አትጉዳ” ሲል ሰማሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች