ምሳሌ 24:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመልካም አመራር ጦርነትን ትመራለህ፥ ብዙ ምክር ባለበትም ድል ይገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጦርነት ለመግጠም መልካም ምክር፣ ድል ለማድረግም ብዙ አማካሪዎች ያስፈልጋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጦርነት ከመሰለፍህ በፊት በጥንቃቄ ዕቅድ ማውጣት ይኖርብሃል፤ ብዙ አማካሪዎች የምታገኝ ከሆነም ማሸነፍህ አይቀርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአስተዳደር ጦርነት ይደረጋል፤ ርዳታም ከምትመክር ልብ ጋር ይሆናል። |
ወይንም በጦርነት ሌላውን ሊጋጠም የሚሄድ ንጉሥ፥ ሃያ ሺህ ሰው አስከትቶ የሚመጣበትን በዐሥር ሺህ ሰው ሊገጥም ይችል እንደሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የማያስብ ማን ነው?