Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 22:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በጌታ ፊት ክፉ አደረገ፤ አባቱም ከሞተ በኋላ የአባቱ አመካሪዎች መጥፊያው እስኪሆኑ ድረስ አማከካሪዎቹ ነበሩና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከአባቱ ሞት በኋላ የአክዓብ ቤት ሰዎች አማካሪዎቹ በመሆን ወደ ጥፋት ስለ መሩት፣ የአክዓብ ቤት እንዳደረገው ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከአባቱ ሞት በኋላ፥ የአክዓብ ቤተሰብ አባላት ለጥፋቱ አማካሪዎቹ ስለ ነበሩ እንደ እነርሱ ክፉ አደረገ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከአ​ባ​ቱም ሞት በኋላ የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ ያጠ​ፉት ዘንድ መካ​ሪ​ዎች ነበ​ሩ​ትና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አባቱም ከሞተ በኋላ የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፤ እስኪጠፉ ድረስ መካሪዎች ነበሩትና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 22:4
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እናቱም ክፉ እንዲያደርግ ትመክረው ነበርና እርሱ ደግሞ በአክዓብ ቤት መንገድ ሄደ።


ልጄ ሆይ፥ ኃጢአተኞች ቢያባብሉህ እሺ አትበል።


የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፥ የክፉዎች ምክር ግን ሽንገላ ነው።


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፥ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።


ልጄ ሆይ፥ ተግሣጽን ከሰማህ በኋላ ከእውቀት ቃል መሳሳትን ተው።


የዖምሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቀሃልና፥ በምክራቸውም ሄዳችኋልና፤ ስለዚህ አንተን ለጥፋት ነዋሪዎቿን ደግሞ ለመዘባበቻ ሰጥቻችኋለሁ፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች