ፌዘኛን ብታስወጣ ክርክር ይቆማል፥ ጠብና ስድብም ያልቃል።
ፌዘኛን አስወጣው፤ ጠብ ይወገዳል፤ ጥልና ስድብም ያከትማል።
ፌዘኛን ሰው ብታስወጣ ጠብ ይቆማል፤ ጠብና ስድብም አይኖሩም።
ነፍሰ ገዳይን ከጉባኤ አውጣ፥ ከእርሱም ጋር ክርክር ይወጣል፥ በጉባኤ በሚቀመጥበት ጊዜ ሁሉን ያዋርዳልና።
ከዋነኛውም ካህን ከኤልያሴብ ልጅ ከዮአዳ ልጆች አንዱ ለሖሮናዊው ለሰንበላጥ አማች ነበረ፥ ከእኔም ዘንድ አባረርሁት።
ባልንጀራውን በቀስታ የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፥ በዓይኑ ትዕቢተኛ፥ በልቡ ኩራተኛ የሆነውን አልታገሥም።
የሰነፍ ከንፈር በጥል ውስጥ ትገባለች፥ አፉም በትርን ትጠራለች።
ኩሩና ተጓዳጅ ሰው ፌዘኛ ይባላል፥ እርሱም በትዕቢት ቁጣ ያደርጋል።
እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ቤተ ክርስቲያንንም ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቁጠረው።
በውጭ ባሉት ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።
እስራኤላውያንም አቤሜሌክ መሞቱን ሲያዩ ወደየቤታቸው ተመለሱ።