ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።
ምሳሌ 13:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፥ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ ድኻው ግን ሥጋት የለበትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብታም በገንዘብ ሕይወቱን ለማዳን ይጣጣራል፤ ድኻ ግን የሚወሰድበት ሀብት ስለሌለው አይጨነቅም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሃ ግን ቍጣን አይቃወምም። |
ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።
በመካከላቸውም እስማኤልን፦ “በእርሻ ውስጥ የተሸሸገ ስንዴና ገብስ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን” የሚሉት ዐሥር ሰዎች ተገኙ። እርሱም ተዋቸው፥ ከወንድሞቻቸውም ጋር አልገደላቸውም።