ምሳሌ 10:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠቢባን እውቀትን ያከማቻሉ፥ የአላዋቂ አፍ ግን ለጥፋት ይቀርባል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠቢባን ዕውቀት ያከማቻሉ፤ የቂል አንደበት ግን ጥፋትን ይጋብዛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠቢባን በሚቻላቸው ዘዴ ሁሉ ዕውቀትን ያከማቻሉ፤ ሞኞች በሚናገሩበት ጊዜ ግን ጥፋት መምጣቱ አይቀርም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠቢብ ዕውቀትን ይሸሽጋል፤ የችኩል አፍ ግን ለጥፋት ይቀርባል። |
“መንግሥተ ሰማያት አንድ ሰው በእርሻ ውስጥ አግኝቶ መልሶ የሸሸገው የተሰወረ መዝገብ ትመስላለች፤ ከደስታውም ብዛት ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጦ ያንን እርሻ ገዛው።