ምሳሌ 1:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግፍ ማትረፍ የሚፈልግ ሁሉ መንገዱ እንዲሁ ነው። የግፉ ባለቤትም ነፍስ ይነጠቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያላግባብ ለጥቅም የሚሯሯጡ ሁሉ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ የሕይወታቸው መጥፊያም ይኸው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕገ ወጥ መንገድ ሀብትን የሚሰበስቡ ሰዎች ያ የሰበሰቡት ሀብት ሕይወታቸውን ያጠፋዋል። በግፍም የሚበለጽጉ ሰዎች ዕድል ፈንታቸው ይኸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ መንገድ ኀጢአትን የሚፈጽሙ ሁሉ ነው። ቅሚያ ነፍሳቸውን ታጠፋለች። |
በምርኮ መካከል አንድ ያማረ የሰናዖር ካባ፥ ሁለት መቶም ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም ኀምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፥ ወሰድኋቸውም፤ እነሆም፥ በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፥ ብሩም ከሁሉ በታች ነው።”
ኢያሱም፦ “ለምን መከራን አመጣህብን? ጌታ ዛሬ መከራን ያመጣብሃል” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው።
ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ፍርዳቸውም ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!