Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 7:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ኢያሱም፦ “ለምን መከራን አመጣህብን? ጌታ ዛሬ መከራን ያመጣብሃል” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ኢያሱም፣ “እንዲህ ያለውን መከራ ለምን አመጣብህን? እነሆ፤ ዛሬ በአንተም ላይ እግዚአብሔር መከራ ያመጣብሃል” አለው። ከዚያም እስራኤል በሙሉ በድንጋይ ወገሩት፤ የቀሩትንም እንደዚሁ ከወገሩ በኋላ በእሳት አቃጠሏቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ኢያሱም “ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ ያመጣህብን ስለምንድን ነው? እነሆ! በአንተም ላይ ዛሬ እግዚአብሔር መከራን ያመጣብሃል!” አለው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ ዓካንን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ ቤተሰቡንም በድንጋይ ወግረው ንብረቱን ሁሉ አቃጠሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ኢያ​ሱም፥ “ለምን አጠ​ፋ​ኸን? ዛሬ እን​ዳ​ጠ​ፋ​ኸን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ያጥ​ፋህ” አለው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ሉት፤ በድ​ን​ጋ​ይም ወገ​ሩ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ኢያሱም፦ ለምን አስጨነቅኸን? እግዚአብሔር ዛሬ ያስጨንቅሃል አለው፥ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፥ በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 7:25
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕቆብም ሌዊንና ስሞዖንን እንዲህ አለ፦ “በዚች አገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ሰዎች የተጠላሁ ታደርጉኝ ዘንድ እኔን አስጨነቃችሁኝ፥ እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፥ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይመቱኛል፥ እኔም ከወገኔ ጋር እጠፋለሁ።”


ከሦስት ወር በኋላ፥ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፥ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።


የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙንም ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ።


በግፍ ማትረፍ የሚፈልግ ሁሉ መንገዱ እንዲሁ ነው። የግፉ ባለቤትም ነፍስ ይነጠቃል።


ትርፍ ለማግኘት የሚሳሳ ሰው የራሱን ቤት ያውካል፥ መማለጃን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።


ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ዝሙት ነው፤ በመካከላችሁ አመንዝራ እንዳይኖር እርሱና እነርሱ በእሳት ይቃጠሉ።


“ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው ልጁን ለሞሌክ ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው።


የካህንም ልጅ ራስዋን በዝሙት ብታረክስ አባትዋን ታረክሰዋለች፤ በእሳት ትቃጠል።


“ተሳዳቢውን ከሰፈሩ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ ይውገረው።


የሚያውኩአችሁ ራሳቸውን ይስለቡ!


የባርነት ምድር ከሆነው ከግብጽ ካወጣህ ከጌታ ከእግዚአብሔር ሊያርቅህ ፈልጎአልና እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው።


ከዚያም እስራኤል ሁሉ ሰምተው ይፈራሉ፤ ከመካከልህም በማንም እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ዳግም አይደረግም።”


ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስደህ፥ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው።


ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩት፤ ክፉውንም ከመካከልህ አስወግድ፤ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።


በእርግጥ በእግዚአብሔር ዘንድ ጽድቅ ነውና፥ መከራን የሚያደርሱባችሁን በመከራ ብድራታቸውን ይከፍላል።


ከመካከላችሁ ማንም የእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት መራራ ሥር በቅሎ እንዳያስጨንቃችሁ፥


እናንተ ግን እርም ካደረጋችሁት በኋላ እርም ከሆነው ነገር ራሳችሁን ጠብቁ፤ እርም ከሆነው አንዳች የወሰዳችሁ እንደሆነ የእስራኤልን ሰፈር የተረገመ ታደርጉታላችሁ፥ ታስጨንቁታላችሁም።


እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የጌታን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል ፈጽሟልና እርሱና የእርሱ የሆነው ነገር ሁሉ በእሳት ይቃጠል።’ ”


ዮናታንም እንዲህ አለ፤ “አባቴ በምድሪቱ ላይ ችግር ፈጥሯል፤ ከዚህ ማር ጥቂት በቀመስሁ ጊዜ ዐይኔ እንዴት እንደ በራ ተመልከቱ!


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች