ዕጣህን ከእኛ ጋር ጣል፥ ለሁላችንም አንድ ከረጢት ይሁን ቢሉ”፥
ከእኛ ጋራ ዕጣህን ጣል፤ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል” ቢሉህ፣
ና ከእኛ ጋር ተባበር፤ በስርቆትና በቅሚያ የምናገኘውን ሀብት በኅብረት እንጠቀምበታለን።”
ዕጣህን ከእኛ ጋር ጣል፤ ለሁላችንም አንድ ከረጢትና አንድ አቁማዳ ይሁንልን” ቢሉ፥
መልካምና ውድ ሀብት ሁሉ እናገኛለን፥ ከምርኮውም ቤታችንን እንሞላለን፥
ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን አርቅ፥
ከዕቡያን ጋር ምርኮ ከመካፈል ከትሑታን ጋር በተዋረደ መንፈስ መሆን ይሻላል።