ዘኍል 9:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደመናውም በማደሪያው ላይ ለብዙ ቀኖች በቈየም ጊዜ እንኳ የእስራኤል ልጆች የጌታን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናው በድንኳኑ ላይ ብዙ ቀን ቢቈይም እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቃሉ እንጂ ተነሥተው አይጓዙም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደመናው በድንኳኑ ላይ ለብዙ ቀኖች ቢቈይ እንኳ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ እዚያው ይቈያሉ እንጂ አይንቀሳቀሱም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመናውም በድንኳኑ ላይ ብዙ ቀን በተቀመጠ ጊዜ የእስራኤል ልጆች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር፤ አይጓዙምም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደመናውም በማደሪያው ላይ ብዙ ቀን በተቀመጠ ጊዜ የእስራኤል ልጆች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር። |
“የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፤ እኔም በዚህ ስፍራ ከቆሙት ጋር ስፍራን እሰጥሃለሁ።”
በጌታ ትእዛዝ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፥ በጌታም ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፤ ደመናው በማደሪያው ላይ ባረፈበት ጊዜያት ሁሉ በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር።
አንዳንድ ጊዜ ደመናው ለጥቂት ቀኖች በማደሪያው ላይ ይቈይ ነበር፤ በዚያ ጊዜ እንደ ጌታ ትእዛዝ በሰፈራቸው ይቀመጡ ነበር፤ እንደ ጌታም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር።