Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 9:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ደመ​ና​ውም በድ​ን​ኳኑ ላይ ብዙ ቀን በተ​ቀ​መጠ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ይጠ​ብቁ ነበር፤ አይ​ጓ​ዙ​ምም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ደመናው በድንኳኑ ላይ ብዙ ቀን ቢቈይም እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቃሉ እንጂ ተነሥተው አይጓዙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ደመናውም በማደሪያው ላይ ለብዙ ቀኖች በቈየም ጊዜ እንኳ የእስራኤል ልጆች የጌታን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ደመናው በድንኳኑ ላይ ለብዙ ቀኖች ቢቈይ እንኳ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ እዚያው ይቈያሉ እንጂ አይንቀሳቀሱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ደመናውም በማደሪያው ላይ ብዙ ቀን በተቀመጠ ጊዜ የእስራኤል ልጆች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር፥ አይጓዙምም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 9:19
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደመ​ናው ካል​ተ​ነሣ ግን ደመ​ናው እስ​ከ​ሚ​ነ​ሣ​በት ቀን ድረስ አይ​ጓ​ዙም ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አዝ​ዞ​ኛ​ልና እን​ዳ​ት​ሞቱ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ሌሊ​ቱ​ንና ቀኑን ሰባት ቀን ተቀ​መጡ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ሥር​ዐት ጠብቁ፤”


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፥ በዚህም ከቆሙት ከእነዚህ ጋር መግባትን እሰጣለሁ።


እንደ ድን​ኳኑ ሥራ​ዎች ሁሉ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ዕቃና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ ይጠ​ብቁ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይሰ​ፍሩ ነበር፤ ደመ​ናው በድ​ን​ኳኑ ላይ በተ​ቀ​መ​ጠ​በት ዘመን ሁሉ በሰ​ፈ​ራ​ቸው ይቀ​መጡ ነበር።


ደመ​ናው ድን​ኳ​ኑን በጋ​ረ​ደ​በት ቀን ቍጥር ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይሰ​ፍሩ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትእ​ዛዝ ይጓዙ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች