ዘኍል 6:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያኖራሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በዚህ ሁኔታ ስሜን በእስራኤላውያን ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም እግዚአብሔር “በዚህ ሁኔታ ስሜን ጠርተው የእስራኤልን ሕዝብ ቢባርኩ፥ እኔም እነርሱን እባርካቸዋለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ይጠራሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ። |
ለራሱ ሕዝብ ይሆን ዘንድ ሊታደገው፥ እግዚአብሔር በፊቱ እንደሄደለት ሕዝብ፥ ለራሱም ስም ያደርግ ዘንድ አሕዛብንና አማልክቶቻቸውን ከፊቱ አሳዶ ታላቅና አስፈሪ ታምራት እንዳደረገለትና ከግብጽም እንደ ተቤዠው እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ያለ በምድር ላይ ማን አለ?
ያቤጽም፦ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ይሁን፤ እንዳይጎዳኝም ከክፋት ጠብቀኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ራሳቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።
ግራ እንደ ተጋባ ሰው፥ ለማዳንም እንደማይችል ኃያል ለምን ትሆናለህ? አንተ ግን፥ አቤቱ! በመካከላችን ነህ፥ እኛም በስምህ ተጠርተናል፤ አትተወን።”