Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 7:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ራሳቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፥ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ እስራኤላውያን ራሳቸውን አዋርደው ከሚያደርጉት ክፉ ነገር በመራቅ ተጸጽተውና ንስሓ ገብተው ወደ እኔ ቢጸልዩ በሰማይ ሆኜ እሰማቸዋለሁ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር እልላቸዋለሁ፤ ምድራቸውም እንደገና ፍሬያማ እንድትሆን አደርጋለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በስሜ የተ​ጠ​ሩት ሕዝቤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አዋ​ር​ደው ቢጸ​ልዩ፥ ፊቴ​ንም ቢፈ​ልጉ፥ ከክፉ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም ቢመ​ለሱ፥ በሰ​ማይ ሆኜ እሰ​ማ​ለሁ፥ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ው​ንም ይቅር እላ​ለሁ፤ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም እፈ​ው​ሳ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢጸልዩ፥ ፊቴንም ቢፈልጉ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ፥ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 7:14
31 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢዮሣፍጥም ፈራ፥ ጌታንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና፤ በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ።


ይሁዳም ጌታን ይፈልግ ዘንድ ተሰበሰበ፤ ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ ጌታን ለመሻት መጡ።


አንተ በሰማይ ሆነህ ስማ፥ የባርያዎችህንና የሕዝብህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፥ የሚሄዱበትንም መልካም መንገድ አሳያቸው፤ ለሕዝብህም ርስት አድርገህ ለሰጠሃት ምድር ዝናብን ስጥ።


በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፥ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለው።


አንተ በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ ስምህን እንዲያውቁ፥ እንደ ሕዝብህም እንደ እስራኤል እንዲፈሩህ፥ ይህም የሠራሁት ቤት በስምህ እንደ ተጠራ እንዲያውቁ፥ እንግዳው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ።


“ፊቴን እሹት” የሚለውን ቃልህን በልቤ አሰብኩኝ፦ አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ።


የሶርያን ሁለቱን ወንዞችና የሶርያን ሶባልን ባቃጠለ ጊዜ ኢዮአብም ተመልሶ ከኤዶማውያን ሰዎች በጨው ሸለቆ ዐሥራ ሁለት ሺህ በገደለ ጊዜ፥


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


በስውር ወይም በጨለማ ምድር አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፦ በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም፤ እኔ ጌታ እውነትን እናገራለሁ ትክክለኛውንም አወራለሁ።


ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፥ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፥ ይላል ጌታ።


ከዘለዓለም እንዳልገዛኸን በስምህም እንዳልተጠራን ሆነናል።


ግራ እንደ ተጋባ ሰው፥ ለማዳንም እንደማይችል ኃያል ለምን ትሆናለህ? አንተ ግን፥ አቤቱ! በመካከላችን ነህ፥ እኛም በስምህ ተጠርተናል፤ አትተወን።”


እነሆ፥ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፥ እፈውሳቸዋለሁም፤ እጅግም የበዛ ሰላምንና እውነትን እገልጥላቸዋለሁ።


በዚያም ወራት በዚያም ጊዜ፥ ይላል ጌታ፥ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ሆነው ይመጣሉ፥ እያለቀሱም መንገዳቸውን ይሄዳሉ፥ አምላካቸውንም ጌታን ይፈልጋሉ።


ባቢሎንን ልንፈውሳት ሞከርን፥ እርሷ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሏልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ አገራችን እንሂድ።


በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለምን አልሆነም?


በሕያውነቴ እምላለሁ ኃጢአተኛው ሰው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ኃጢአተኛው እንዲሞት አልፈቅድም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ቤት ሆይ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ስለ ምንስ ትሞታላችሁ? በላቸው።


አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የሕዝብህን ልጆች እንዲህ በላቸው፦ በበደለበት ቀን የጻድቅ ጽድቁ አያድነውም፥ ኃጢአተኛም ከኃጢአቱ በተመለሰበት ቀን በኃጢአቱ አይሰናከልም፤ ጻድቁም ኃጢአት በሠራበት ቀን በጽድቁ በሕይወት አይኖርም።


እነርሱም ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያኖራሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።”


ጌታም “ተነሥተህ ቅን ወደ ሚባለው መንገድ ሂድ፤ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰው ፈልግ፤


የምድር አሕዛብም ሁሉ በጌታ ስም መጠራትህን ያያሉ፤ ይፈሩሃልም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች