ዘኍል 6:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሮንንና ልጆቹን እንዲህ በላቸው፤ ‘እስራኤላውያንን በምትባርኩበት ጊዜ እንዲህ በሏቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አሮንና ልጆቹ የእስራኤልን ሕዝብ በሚባርኩበት ጊዜ እንዲህ በሉ ብለህ ንገራቸው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፤ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦ |
ስለዚህ በዚያን ቀን እንዲህ ሲል ባረካቸው፤ “እስራኤላውያን በሚመርቁበት ጊዜ የእናንተን ስም በማስታወስ፥ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ’ ይላሉ።”
የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ከሁሉ በላይ የተቀደሰ እንዲሆን ተለየ፥ እርሱና ልጆቹ፥ ለዘለዓለም በጌታ ፊት እንዲያጥኑና እንዲያገለግሉ፥ በስሙም ለዘለዓለም እንዲባርኩ ተለይተው ነበር።
በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁ፥ በሮሜ ላላችሁ ሁሉ፥ ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
በዚያን ጊዜ የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት እንዲሸከም፥ እርሱንም ለማገልገል በጌታ ፊት እንዲቆም፥ በስሙም እንዲባርክ ጌታ እስከ ዛሬ ድረስ የሌዊን ነገድ ለየ።
እንዲያገለግሉና በጌታ ስም እንዲባርኩ፥ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጉዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፥ አምላክህ ጌታ መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ።
የእስራኤልንም ሕዝብ አስቀድሞ እንዲባረኩ የጌታ ባርያ ሙሴ እንዳዘዘ፥ እስራኤል ሁሉ፥ ሽማግሌዎቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ፈራጆቻቸውም፥ የአገሩ ተወላጆችም፥ መጻተኞችም፥ እኩሌቶቹ በገሪዛን ተራራ ፊት ለፊት እኩሌቶቹም በጌባል ተራራ ፊት ለፊት ሆነው፥ የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት በተሸከሙት በሌዋውያን ካህናት ፊት ለፊት፥ በታቦቱም ፊት በወዲህና በወዲያ ቆመው ነበር።
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ያወቃችሁ፥ በመንፈስ የተቀደሳቹ፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ትታዘዙና በደሙም ትረጩ ዘንድ ለተመረጣችሁት፥ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።