ዘኍል 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የመብራቱንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መቆንጠጫዎቹንም፥ መተርኮሻዎቹንም፥ ዘይቱንም የሚያቀርቡባቸውን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ደግሞም ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው ማብሪያ መቅረዙንና መብራቶቹን፣ መኰስተሪያዎቹንና የኵስታሪ መቀበያዎቹን፣ እንዲሁም ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉትን የዘይት ዕቃዎች ይሸፍኑበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው መቅረዙን፥ ከነመብራቶቹ ከመኮስተሪያዎቹና ከኩስታሪ ማኖሪያዎቹ፥ እንዲሁም ከዘይት ዕቃዎቹ ሁሉ ጋር ይሸፍኑት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፤ የሚያበሩባትንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎችዋንም፥ መኰስተሪያዎችዋንም፥ የኵስታሪ ማድረጊያዎችዋንም፥ እርስዋንም ለማገልገል የዘይቱን ማሰሮዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የሚያበራውንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መኰስተሪያዎቹንም፥ የኩስታሪ ማድረጊያዎቹንም፥ እርሱንም ለማገልገል የዘይቱን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤ |
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።”