Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 4:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሰማ​ያ​ዊ​ው​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይው​ሰዱ፤ የሚ​ያ​በ​ሩ​ባ​ት​ንም መቅ​ረዝ፥ ቀን​ዲ​ሎ​ች​ዋ​ንም፥ መኰ​ስ​ተ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ የኵ​ስ​ታሪ ማድ​ረ​ጊ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ እር​ስ​ዋ​ንም ለማ​ገ​ል​ገል የዘ​ይ​ቱን ማሰ​ሮ​ዎች ሁሉ ይሸ​ፍኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ደግሞም ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው ማብሪያ መቅረዙንና መብራቶቹን፣ መኰስተሪያዎቹንና የኵስታሪ መቀበያዎቹን፣ እንዲሁም ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉትን የዘይት ዕቃዎች ይሸፍኑበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የመብራቱንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መቆንጠጫዎቹንም፥ መተርኮሻዎቹንም፥ ዘይቱንም የሚያቀርቡባቸውን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው መቅረዙን፥ ከነመብራቶቹ ከመኮስተሪያዎቹና ከኩስታሪ ማኖሪያዎቹ፥ እንዲሁም ከዘይት ዕቃዎቹ ሁሉ ጋር ይሸፍኑት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የሚያበራውንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መኰስተሪያዎቹንም፥ የኩስታሪ ማድረጊያዎቹንም፥ እርሱንም ለማገልገል የዘይቱን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 4:9
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ በአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት መሸ​ፈኛ ውስጥ ያድ​ርጉ፤ በመ​ሸ​ከ​ሚ​ያ​ውም ላይ ያድ​ር​ጉት።


በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ቀይ መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ርጉ፤ በአ​ቆ​ስ​ጣ​ውም ቍር​በት መሸ​ፈኛ ይሸ​ፍ​ኑት። መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ያግቡ።


መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል፤በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።


በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች