105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።
105 ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው።
105 ቃልህ እንደ መብራት ይመራኛል፤ ለመንገዴም ብርሃን ነው።
ትእዛዝ መብራት፥ ትምህርትም ብርሃን ነውና፥ የተግሣጽም ዘለፋ የሕይወት መንገድ ነውና፥
ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፥ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።
አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዐይን ግን ታዋርዳለህ።
ደግሞም ይህን የበለጠ የሚያረጋግጥ የነቢያት ቃል አለ፤ ጎሕ እስኪቀድ ድረስ የንጋትም ኮከብ በልባችሁ እስኪገለጥ፥ ሰው በጨለማ ስፍራ የሚበራን መብራት እንደሚያስተውል ቃሉን ልብ በማለት መልካም ታደርጋላችሁ።
በራሴ ላይ መብራቱ በበራ ጊዜ፥ እኔም ጨለማውን አልፌ በብርሃኑ በሄድሁ ጊዜ፥
ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤
የጌታ ሕግ ፍጹም ነው፥ ነፍስን ይመልሳል፥ የጌታ ምስክር የታመነ ነው፥ የዋሆችን ጠቢባን ያደርጋል።