ዘኍል 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰፈሩ ለመጓዝ በተነሣ ጊዜ አሮንና ልጆቹ ገብተው የሚሸፍነውን መጋረጃ ያውርዱ፥ የምስክሩንም ታቦት ይሸፍኑበት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰፈሩ ሲነሣ አሮንና ልጆቹ ገብተው የሚከልለውን መጋረጃ ያውርዱ፤ የምስክሩንም ታቦት ይጠቅልሉበት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሕዝቡ ከሰፈረበት ቦታ በሚነሣበት ጊዜ አሮንና ልጆቹ ወደ ድንኳኑ ገብተው፥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ያለውን መጋረጃ በማውረድ የኪዳኑን ታቦት በእርሱ ይጠቅልሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰፈሩ በተነሣ ጊዜ አሮንና ልጆቹ ገብተው የሚሸፍነውን መጋረጃ ያወርዳሉ፤ የምስክሩንም ታቦት ይጠቀልሉበታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰፈሩ በተነሡ ጊዜ አሮንና ልጆቹ ገብተው የሚሸፍነውን መጋረጃ ያውርዱ፥ የምስክሩንም ታቦት ይጠቅልሉበት፤ |
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመናው ውስጥ እታያለሁና፥ እንዳይሞት በመጋረጃው ውስጥ በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ወደተቀደሰው ስፍራ፥ ሁልጊዜ እንዳይገባ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።
አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃዎች ሁሉ መሸፈናቸውን በጨረሱ ጊዜ፥ ሰፈሩም ለመጓዝ ሲነሣ፥ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ከዚያም በኋላ ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። የቀዓት ልጆች የሚሸከሙአቸው የመገናኛው ድንኳን ዕቃዎች እነዚህ ናቸው።
ጌታም ከቤትሼሜሽ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ምክንያቱም ወደ ጌታ ታቦት ውስጥ በመመልከታቸው ነበር። ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ ጌታ እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሱ።