እኛ ሁላችን መሞታችን አይቀሬ ነው፤ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር የተሰደደ ሰው በስደት በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።
ዘኍል 35:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማኅበሩም ነፍሰ ገዳዩን ከደም ተበቃዩ እጅ ያድነዋል፥ ማኅበሩም ወደ ሸሸበት ወደ መማፀኛ ከተማ ይመልሰዋል፤ በቅዱስ ቅባትም የተቀባው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያ ይቀመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኅበሩም በነፍሰ ገዳይነት የተከሰሰውን ሰው ከደመኛው እጅ በማስጣል ወደ ሸሸበት ወደ መማጸኛው ከተማ ይመልሰው፤ የተቀደሰ ዘይት የተቀባው ሊቀ ካህን እስኪሞትም ድረስ በዚያ ይቈይ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማኅበሩ በግድያ ወንጀል የተከሰሰውን ሰው ከተበቃይ እጅ በመታደግ አምልጦ ወደነበረበት ወደ መማጠኛ ከተማዋ መመለስ አለበት፤ በዘመኑ ሊቀ ካህናት የሆነው ሰው እስከሚሞትበት ድረስ እዚያው መቈየት ይኖርበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማኅበሩም ነፍሰ ገዳዩን ከባለ ደሙ እጅ ያድኑታል፤ ማኅበሩም ወደ ሸሸበት ወደ መማፀኛው ከተማ ይመልሱታል፤ በቅዱስ ዘይትም የተቀባው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያ ይቀመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኅበሩም ነፍሰ ገዳዩን ከደም ተበቃዩ እጅ ያድነዋል፥ ማኅበሩም ወደ ሸሸበት ወደ መማፀኛ ከተማ ይመልሰዋል፤ በቅዱስ ዘይትም የተቀባው ዋነኛው ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያ ይቀመጣል። |
እኛ ሁላችን መሞታችን አይቀሬ ነው፤ በመሬት ላይ እንደ ፈሰሰና ተመልሶም ሊታፈስ እንደማይችል ውሃ ነን፤ እግዚአብሔር የተሰደደ ሰው በስደት በዚያው እንዳይቀር የሚመለስበትን ሁኔታ ያመቻቻል እንጂ ሕይወቱ እንድትጠፋ አይፈቅድም።
“በራሱም ላይ የቅባዓት ዘይት የፈሰሰበት፥ የክህነትም ልብስ እንዲለብስ የተቀደሰው፥ ከወንድሞቹ ይበልጥ ከፍ ያለው ካህን የራሱን ጠጉር አያጐስቁል ልብሱንም አይቅደድ።
ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በመማፀኛው ከተማ ውስጥ መቀመጥ ይገባው ነበርና። ታላቁ ካህን ከሞተ በኋላ ግን ነፍሰ ገዳዩ ወደ ርስቱ ምድር ይመለሳል።
በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቆም ድረስ፥ በዚያም ወራት ያለው ታላቁ ካህን እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቀመጥ፤ ከዚያም ወዲያ ነፍሰ ገዳዩ ይመለሳል፥ ወደ ከተማውም ወደ ቤቱም ሸሽቶ ወደ ወጣበትም ከተማ ይገባል።’ ”