አቤሴሎም፥ “ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም” በማለት መታሰቢያ እንዲሆነው በሕይወት እያለ የንጉሥ ሸለቆ በተባለው ስፍራ ለራሱ ሐውልት አቁሞ ስለ ነበር፥ እስከ ዛሬ ድረስ የአቤሴሎም ሐውልት ተብሎ ይጠራል።
ዘኍል 32:42 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኖባህም ሄደ ቄናትንም መንደሮቻቸውንም ያዘ፥ እነርሱንም በስሙ ኖባህ ብሎ ጠራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ኖባህ ቄናትንና በዙሪያዋ ያሉትን መንደሮች በመያዝ በራሱ ስም፣ ኖባህ ብሎ ጠራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኖባሕ ደግሞ በቄናትና በመንደሮችዋ ላይ አደጋ በመጣል ወሰዳቸው፤ በራሱም ስም “ኖባሕ” ብሎ ሰየማቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናባውም ሄዶ ቄናትንም፥ መንደሮችዋንም ወሰደ፤ በስሙም ናቦት ብሎ ጠራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኖባህም ሄደ ቄናትንም መንደሮችዋንም ወሰደ፥ በስሙም ኖባህ ብሎ ጠራቸው። |
አቤሴሎም፥ “ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም” በማለት መታሰቢያ እንዲሆነው በሕይወት እያለ የንጉሥ ሸለቆ በተባለው ስፍራ ለራሱ ሐውልት አቁሞ ስለ ነበር፥ እስከ ዛሬ ድረስ የአቤሴሎም ሐውልት ተብሎ ይጠራል።
ከዚያም ጌዴዎን ተነሣ፤ ከኖባህና ከዮግብሃ በስተ ምሥራቅ የሚኖሩ ዘላኖች የሚሄዱበትን መንገድ ተከትሎ በጠላት ሠራዊት ላይ በድንገት አደጋ ጣለ።