መሳፍንት 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ከዚያም ጌዴዎን ተነሣ፤ ከኖባህና ከዮግብሃ በስተ ምሥራቅ የሚኖሩ ዘላኖች የሚሄዱበትን መንገድ ተከትሎ በጠላት ሠራዊት ላይ በድንገት አደጋ ጣለ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ከዚያም ጌዴዎን ተነሣ፤ ከኖባህና ከዮግብሃ በስተምሥራቅ የሚኖሩ ዘላኖች የሚሄዱበትን መንገድ ተከትሎ በጠላት ሰራዊት ላይ በድንገት አደጋ ጣለ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ስለዚህ ጌዴዎን በበረሓው መንገድ አድርጎ በኖባሕና በዮግበሃ ምሥራቅ በኩል ወጣና የጠላት ሠራዊት ሳያስበው በመዝናናት ላይ እያለ አደጋ ጣለበት። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ጌዴዎንም በድንኳን የሚኖሩ ሰዎች ባሉበት መንገድ በኖቤትና በዮግቤል በምሥራቅ በኩል ወጣ፤ ሠራዊቱም ተዘልሎ ሳለ አጠፋቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ጌዴዎንም የድንኳን ተቀማጮች ባሉበት መንገድ በኖባህና በዮግብሃ በምሥራቅ በኩል ወጣ፥ ሠራዊቱም ተዘልሎ ነበርና ሠራዊቱን መታ። ምዕራፉን ተመልከት |