ኢዮሣፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፥ በዘበዙትም፥ ሁሉንም ለመሸከም አልቻሉም፤ ከምርኮውም ብዛት የተነሣ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ይበዘብዙ ነበር።
ዘኍል 31:53 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወታደሮቹም ሁሉ ከምርኮአቸው ለራሳቸው ወሰዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱም ወታደር ለራሱ የወሰደው ምርኮ ነበረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጦር ሹማምንት ያልሆኑት ወታደሮች ግን ያመጡትን ምርኮ ለራሳቸው አስቀሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ የማረኩትን ለየራሳቸው ወሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎች ሁሉ ከምርኮአቸው ለራሳቸው ወሰዱ። |
ኢዮሣፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፥ በዘበዙትም፥ ሁሉንም ለመሸከም አልቻሉም፤ ከምርኮውም ብዛት የተነሣ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ይበዘብዙ ነበር።
ነገር ግን ሴቶቹን ሕፃናትን፥ እንስሳቱንና በከተማዪቱ ውስጥ የሚገኘውን ማናቸውንም ነገር በምርኮ ለራስህ አድርግ አምላክህ ጌታ ከጠላቶችህ የሚሰጥህን ምርኮ ልትጠቀምበት ትችላለህ።