Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 20:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ነገር ግን ሴቶቹን ሕፃናትን፥ እንስሳቱንና በከተማዪቱ ውስጥ የሚገኘውን ማናቸውንም ነገር በምርኮ ለራስህ አድርግ አምላክህ ጌታ ከጠላቶችህ የሚሰጥህን ምርኮ ልትጠቀምበት ትችላለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ነገር ግን ሴቶቹን ሕፃናትን፣ እንስሳቱንና በከተማዪቱ ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውንም ነገር በምርኮ ለራስህ አድርግ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከጠላቶችህ የሚሰጥህን ምርኮ ልትጠቀምበት ትችላለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሆኖም ሴቶችንና ሕፃናት ልጆችን፥ እንስሶችንና በከተማይቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ሁሉ ለራስህ ማርከህ ትወስዳለህ፤ የጠላቶችህ ንብረት የሆነውን ሁሉ ልትጠቀምበት ትችላለህ፤ እግዚአብሔር አምላክህ እርሱን ለአንተ አሳልፎ ሰጥቶሃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከሴ​ቶ​ቹና ከጓዙ በቀር እን​ስ​ሶ​ቹን፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ያለ​ውን ምርኮ ሁሉ ዘር​ፈህ ለአ​ንተ ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሰ​ጥ​ህን የጠ​ላ​ቶ​ች​ህን ምርኮ ትበ​ላ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነገር ግን ሴቶቹንና ሕፃናትን እንስሶቹንም በከተማይቱም ያለውን ምርኮ ሁሉ በዝብዘህ ለአንተ ትወስዳለህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር የሚሰጥህን የጠላቶችህን ምርኮ ትበላለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 20:14
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ ምርኮዋንና ከብትዋን ግን ለራሳችሁ ትዘርፋላችሁ፤ ከከተማይቱም በስተ ኋላ ድብቅ ጦር አስቀምጥ።”


እንዲህም አላቸው፦ “በብዙ ሀብት እጅግም ብዙ በሆነ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ እጅግም ብዙ በሆነ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”


የእስራኤልም ልጆች የምድያምን ሴቶችና ልጆቻቸውን ማረኩ፤ እንስሶቻቸውንና መንጎቻቸውንም ዕቃቸውንም ሁሉ በዘበዙ።


በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።


ጌታ ትእዛዙን ሰጠ፥ የሚያበሥሩት ብዙ ሠራዊት ናቸው።


ኢዮሣፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፥ በዘበዙትም፥ ሁሉንም ለመሸከም አልቻሉም፤ ከምርኮውም ብዛት የተነሣ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ይበዘብዙ ነበር።


የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፥ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አላስቀሩም።


ወንድን በመኝታ የማያውቁትን ሴቶች ልጆችን ሁሉ ግን ለራሳችሁ በሕይወት አቆዩዋቸው።


የማረኩአቸውንም ሰዎች ምርኮውንና ብዝበዛውን፥ በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ወዳለው ሰፈር፥ ወደ ሙሴና ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር አመጡ።


የሰውንና የእንስሳን ምርኮና ብዝበዛ ሁሉ ወሰዱ።


ሙሴም አላቸው፦ “በውኑ ሴቶችን ሁሉ በሕይወት እንዲኖሩ ፈቀዳችሁላቸውን?


እንግዲህ የአካባቢህ አሕዛብ ከተሞች ባልሆኑትና ከአንተ እጅግ ርቀው በሚገኙት ከተሞች ሁሉ ላይ የምታደርገው ይኸው ነው።


ከብቶቻቸውንና ከከተሞቻቸው ያገኘነውን ምርኮ ግን ለራሳችን ወሰድን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች