ዘኍል 31:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድያማውያኑ የሚኖሩባቸውን ከተሞች ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም በሙሉ አቃጠሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተሞቻቸውንና የሰፈሩበትን ቦታ ሁሉ አቃጠሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ፥ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀመጡባቸውን ከተሞቻቸውን ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ። |
ቀደም ሲል የግብጽ ንጉሥ በጌዜር ላይ አደጋ ጥሎ፥ ነዋሪዎችዋን ከነዓናውያንን ገድሎ ከተማይቱንም አቃጥሎ በቁጥጥሩ ሥር አድርጓት ነበር፤ ከዚያም በኋላ ሴት ልጁን ለሰሎሞን በዳረለት ጊዜ የጌዜርን ከተማ ማጫ አድርጎ ሰጣት።
ስለዚህም ሞትና ኀዘን፥ ራብም የሆኑት መቅሰፍቶችዋ በአንድ ቀን ይመጣሉ፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።”
በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ጺቅላግ ደረሱ፤ በዚህ ጊዜ አማሌቃውያን ደቡቡን አገርና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ ጺቅላግንም ወግተው አቃጥለው ነበር።