በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው።
ዘኍል 3:47 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለእያንዳንዱ አምስት ሰቅል ውሰድ፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ትወስዳለህ፤ ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለእያንዳንዱ በኵር ክብደቱ ባለሃያ አቦሊ በሆነው በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ልክ ዐምስት ዐምስት ሰቅል ተቀበል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለያንዳንዱ መዋጃ በመቅደሱ ሚዛን መሠረት አምስት ሰቅል የሚመዝን ብር ትወስዳለህ፤ አንዱ ሰቅል ኻያ ጌራ ነው (ጌራ 0.6 ግራም ነው)። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በየራሱ አምስት ዲድርክም ውሰድ፤ እንደ መቅደሱ ዲድርክም ብዛት ትወስዳለህ፤ ዲድርክም ሃያ አቦሊ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ትወስዳለህ፤ ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ነው። |
በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው።
ለመቅደሱ ሥራ የተደረገው ወርቅ ሁሉ፥ የተሰጠው ወርቅ በሙሉ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ሀያ ዘጠኝ መክሊት ሰባት መቶ ሠላሳ ሰቅል ነበረ።
ከአንድ ወር ጀምሮ የምትዋጀውን እንደ ግምትህ ትዋጀዋለህ፤ ግምቱም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን አምስት ሰቅል ይሆናል፤ እርሱም ሀያ አቦሊ ነው።
መባውም ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ጐድጓዳ ሳሕን፤