Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 መባውም ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ጐድጓዳ ሳሕን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስጦታውም፣ እያንዳንዱ ለእህል ቍርባን የሚሆን በዘይት የተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን የብር ሳሕንና ሰባ ሰቅል የሚመዝን ከብር የተሠራ ጐድጓዳ ሳሕን፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ያቀረባቸውም መባዎች እነዚህ ናቸው፦ በመቅደሱ ሚዛን መሠረት መቶ ሠላሳ ሰቅል የሚመዝን አንድ ከብር የተሠራ ዝርግ ሳሕን፥ ከሰባ ሰቅል ብር የተሠራ አንድ ጐድጓዳ ሳሕን፥ ሁለቱም ለእህል ቊርባን በሚሆን ከዘይት ጋር በተቀላቀለ ደቃቅ ዱቄት የተሞሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 መባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 7:13
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በቆጠራው የሚያልፉ ሁሉ ይህን ይስጡ፥ በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት ግማሽ ሰቅል ይሰጣል፥ ሰቅል ሃያ ጌራ ነው፤ ግማሽ ሰቅል ለጌታ ስጦታ ነው።


“ማናቸውም ሰው የእህል ቁርባን ለጌታ ሲያቀርብ ቁርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስበታል፥ ዕጣንም ይጨምርበታል፤


በገበታው ላይ የሚኖሩትን ዕቃዎች፥ ወጭቶቹን፥ ጭልፋዎችን፥ ጽዋዎችንና ለማፍሰሻ የሚሆኑ መቅጃዎችን፥ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።


ለማፍሰሻም እንዲሆኑ ወጭቶችዋን ጭልፋዎችዋንም መቅጃዎችዋንም ጽዋዎችዋንም አድርግ፤ እነርሱንም ከጥሩ ወርቅ አድርጋቸው።


ራሱን በሳሕን መጥቶ ለልጅቱ ተሰጣት፤ እርሷም ወደ እናትዋ ወሰደችው።


እርሷም በእናትዋ ተመክራ “የመጥምቁን የዮሐንስን ራስ በዚህ ሳሕን አሁን ስጠኝ” አለችው።


በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኩራ ላይ፦ “ለጌታ የተቀደሰ” ተብሎ ይጻፋል። በጌታም ቤት ያሉ ምንቸቶች በመሠዊያው ፊት እንዳሉ ዳካዎች ይሆናሉ።


የዘበኞቹም አለቃ ወጭቶቹንና ማንደጃዎቹን፥ ጐድጓዳ ሳሕኖቹንና የሸክላ ድስቶቹን፥ መቅረዞችንና ሙዳዮችን መንቀሎችንም፥ የወርቁን ዕቃ በወርቅ፥ የብሩንም ዕቃ በብር አድርጎ፥ ወሰደ።


ንጉሡ፥ አማካሪዎቹ፥ ባለሥልጣናቱ በዚያም የተገኙት እስራኤል ሁሉ፤ ለአምላካችን ቤት የሰጡትን የብሩንና፥ የወርቁን፥ የዕቃውንም ስጦታ መዝኜ ሰጠኋቸው።


ድስቶቹ፥ መጫሪያዎቹና ጐድጓዳ ሳሕኖቹ፤ ለጌታ ቤት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሑራም እነዚህን ሁሉ ዕቃዎች ለሰሎሞን የሠራለት ከተወለወለ ንጹሕ ነሐስ ነበር።


ዐሥሩ ባለ መንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎች፥ ዐሥሩ የመታጠቢያ ገንዳዎች።


ለእያንዳንዱ አምስት ሰቅል ውሰድ፤ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ትወስዳለህ፤ ሰቅሉም ሀያ አቦሊ ነው።


ግምትህም ሁሉ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ይሆናል፤ ሰቅሉ ሀያ አቦሊ ይሆናል።


ለወንድ ከሃያ ዓመት ጀምሮ እስከ ስልሳ ዓመት ድረስ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን ግምትህ ኀምሳ የብር ሰቅል ይሁን።


በመጀመሪያውም ቀን መባውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።


ዕጣንም የተሞላ ሚዛኑ ዐሥር ሰቅል የሆነ አንድ የወርቅ ሙዳይ፤


መባውም ለእህል ቁርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ ጐድጓዳ ሳሕን፤


ቁርባኑን ለማቅረብ የሚያመጣ ሰው የኢን መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ አንድ እጅ የሆነ መልካም ዱቄትን የእህል ቁርባን አድርጎ ለጌታ ያቅርብ፤


የኢንም መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ተወቅጦ በተጠለለ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቁርባን ታቀርባለህ።


በወሩ መባቻ ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን፥ ከመጠጡም ቁርባን ሌላ፥ እንደ ሕጋቸው ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርቡ ናቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች